ጾመ ሐዋርያት

ጾመ ሐዋርያት

ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን...
በዓለ ጰራቅሊጦስ

በዓለ ጰራቅሊጦስ

በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው። ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ የግሪክ ነው። “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም መጽንኢ (በእምነት የሚያጸና)፣ መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ)፣ ናዛዚ (ያዘኑትን የሚያረጋጋ)፣ መስተፍስሒ (የተጨነቁትን...
በእንተ ዕርገት

በእንተ ዕርገት

ከመምህር በትረማርያም አበባው (የትርጓሜ መምህር) የተወሰደ ዕርገት ዐርገ ዐረገ፣ ወጣ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ወደ ላይ መውጣት ማለት ነው፡፡ “ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ” (መሳ.፲፫፥፳) ከዚህ እንደምናየው ዐረገ ማለት ወደ ላይ ወጣ ማለት ነው፡፡ ይህ ቃላዊ ትርጓሜው ሲሆን ምሥጢራዊው ትርጓሜ ግን ዕርገት ማለት የሰው...
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ፣ የዜማ ደራሲና ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ድንቅ ተጋድሎን ፈጽሞ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ግንቦት ፲፩ የከበረች እንደመሆኗ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡ ቅዱስ ያሬድ የተወለደው ሚያዝያ ፭ ቀን በ፭፻፭ ዓ.ም በአክሱም ከተማ ነው፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይስሐቅ ይባላል፤ እናቱ ደግሞ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ትባላለች። አባቱ የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡ የሞተው ቅዱስ...
ሰሙነ ሕማማት 

ሰሙነ ሕማማት 

ሰሙነ ሕማማት ተብሎ የሚጠራው ወቅት ከዐቢይ ጾም መጨረሻ ከሆሣዕና ዋዜማ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ባሉት ቀናት ውስጥ ያለው ሳምንት ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ይህንን ወቅት አስመልክቶ  በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ‹‹ውእቱ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ፤ እርሱ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤›› በማለት የነገረ ሕማማቱን ምሥጢር አስቀድሞ ተናግሮአል፡፡ በዚህም መሠረት በኋለኛው ዘመን እግዚአብሔር ወልድ ስለኛ ስለ ሰው...
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት

እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡   የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ  አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት፤ በነቢያት  ሲነገር፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማእከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን...
ለቀዳማዊ ልደት አመሥጠሮ፤ ወለካልዑ ልደት አመንከሮ

ለቀዳማዊ ልደት አመሥጠሮ፤ ወለካልዑ ልደት አመንከሮ

   እንኳን ለብርሃነ ልደቱ ወጥምቀቱ አደረሳችሁ፤                ለቀዳማዊ ልደት አመሥጠሮ፤ ወለካልዑ ልደት አመንከሮ፤                   ቀዳማዊ ልደቱን ረቂቅ፣ ደኃራዊ ልደቱን ድንቅ አደረገው፡፡ እግዚአብሔር በሰው መካከል ያደረገውንና ለሰው የገለጠውን ነገር ስናስበው አስደናቂና የማይደረስበት ሆኖ እናገኘዋለን፤ ጥንት ሲፈጥረው ጀምሮ ክብርት ዓርአያውን፣ ቅድስት ምሳሌውን ሰጥቶ ሲፈጥረው ከሁሉም የተለየ...