ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ፣ የዜማ ደራሲና ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ድንቅ ተጋድሎን ፈጽሞ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ግንቦት ፲፩ የከበረች እንደመሆኗ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡ ቅዱስ ያሬድ የተወለደው ሚያዝያ ፭ ቀን በ፭፻፭ ዓ.ም በአክሱም ከተማ ነው፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይስሐቅ ይባላል፤ እናቱ ደግሞ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ትባላለች። አባቱ የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡ የሞተው ቅዱስ...