by Biranna Tech | May 31, 2026 | በዓላት
በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው። ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ የግሪክ ነው። “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም መጽንኢ (በእምነት የሚያጸና)፣ መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ)፣ ናዛዚ (ያዘኑትን የሚያረጋጋ)፣ መስተፍስሒ (የተጨነቁትን...
by Biranna Tech | May 21, 2026 | በዓላት, ወቅታዊ
ከመምህር በትረማርያም አበባው (የትርጓሜ መምህር) የተወሰደ ዕርገት ዐርገ ዐረገ፣ ወጣ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ወደ ላይ መውጣት ማለት ነው፡፡ “ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ” (መሳ.፲፫፥፳) ከዚህ እንደምናየው ዐረገ ማለት ወደ ላይ ወጣ ማለት ነው፡፡ ይህ ቃላዊ ትርጓሜው ሲሆን ምሥጢራዊው ትርጓሜ ግን ዕርገት ማለት የሰው...
by Biranna Tech | Jan 6, 2026 | በዓላት, ትምህርተ ሃይማኖት
እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት፤ በነቢያት ሲነገር፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማእከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን...
by Biranna Tech | Jan 6, 2026 | በዓላት, ትምህርተ ሃይማኖት, ወቅታዊ
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ ወጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ ለቀዳማዊ ልደት አመሥጠሮ፤ ወለካልዑ ልደት አመንከሮ፤ ቀዳማዊ ልደቱን ረቂቅ፣ ደኃራዊ ልደቱን ድንቅ አደረገው፡፡ እግዚአብሔር በሰው መካከል ያደረገውንና ለሰው የገለጠውን ነገር ስናስበው አስደናቂና የማይደረስበት ሆኖ እናገኘዋለን፤ ጥንት ሲፈጥረው ጀምሮ ክብርት ዓርአያውን፣ ቅድስት ምሳሌውን ሰጥቶ ሲፈጥረው ከሁሉም የተለየ...